
ብዙአየሁ ታደለ እና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን ላለፉት አምስት ዓመታት በላይ በድህነት ቅነሳ፣ መሠረታዊ ትምህርት እገዛ፣ በቤት ልማት፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በተፈጥሮ እና በሰው ሠራሽ አደጋ ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች የፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ፣ ለወጣቶች እና ለሴቶች የሥራ እድል ፈጠራ፣ እንዲሁም ለአረጋውያን ድጋፍ በመላው የአገሪቱ ክፍል በራስ ተነሣሽነት እና ከመንግሥት የሚመጡ ጥሪዎችን በመቀበል የበጎ አድራጎት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ድርጅት ነው፣