- Administrator
- Projects
- Hits: 601
ለጌጃ ልማት ተነሺዎች ገንብተን ባስረከብናቸው ሱቆች የንግድ ስራዎች ተጀምረዋል፡፡
- Administrator
- Projects
- Hits: 601
ለጌጃ ልማት ተነሺዎች ገንብተን ባስረከብናቸው ሱቆች የንግድ ስራዎች ተጀምረዋል፡፡
ቡዙአየሁ ታደለ እና ቤተሰቦቹ ፋውንዴሽን ከገነባቸው ከእነዚህ ሱቆች በልማት ተነሺ ከሆኑት ውጪ በአከባቢው በጉሊት ስራ ይተዳደሩ የነበሩ እናቶችም ባለሱቅ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡
ለአከባቢው ነዋሪዎች የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች ፤ አትክልትና ፍራፍሬ፤ የአዋቂና ህጻናት አልባሳት ፤ የፕላሰቲክ ውጤቶችን በማቅረብና የልብስ ስፌት አግልግሎት እየሰጡ እራሰቸውንና የአከባቢውን ነዋሪዎች እየጠቀሙ ይገኛሉ፡፡
የእነዚህ 10 ሱቆች መገንባት በአከባቢው ይኖሩ የነበሩ ሴቶችና አቅመ ደካሞች በንግድ ስራ ተሰማርተው ራሳቸውን እንዲችሉ አስችሏል፡፡
ፋውንዴሽኑ በጠቅላላው 1.5 ሚሊዮን ብር ወጪ አድርጎ ሱቆቹን አስገንብቶ በቅርቡ ለልደታ ከተማ ክፍለ ከተማ ማስረከቡ ይታወሳል።